- Target:
- EBS (Ethiopian Broadcasting TV), Ethiopian orthodox church patriarch
- Region:
- GLOBAL
የሀገራችን ሕግ መንግስት ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብት እንዳለው በግልጽ አስቀምጧል :: ስለዚህ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት ያለ ተጽዕኖና ግፊት መከተል ይችላል :: የሚያምንበትንም ሃይማኖት ፣ የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መሰረት ማስተማርና ማስፋፋትን የሚከለክለው የለም::
ነገር ግን የሌሎችን የእምነት ተቋማትን ስም በማናለብኝነት በመዝረፍና በዛ እምነት ስም ስብከትም ሆነ ትምህርት በብዙሃን መገናኛ ማስተላለፍ ግን ወንጀልም ፣ሀጥያትም ነው::
ለዚህ አባባላችን መነሻ የሆነው በኢቢኤስ ላይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የሚተላለፉ ቃለ አዋዲና ታዖሎጎስ የተባሉ የቴሌቪዝን መርሓ ግብሮች ናቸው:: እነዚህ መርሓ ግብሮች ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደንብ መሠረት የተዘጋጁ እንደሆኑ ይገልጻሉ:: ነገር ግን የሚተላለፉት ዝግጅቶች ግን ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አንጻር ብዙ ጥያቄ የሚያስነሱና የብዙውን ኦርቶዶክሳዊ ግንባር የሚያስቋጥሩ ናቸው:: በነዚህ መርሓ ግብሮች የሚራቀቁት ጥቂት የማይባሉት ሰባክያንም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የኑፋቄ ትምህርት ሲጽፉና ሲያስፋፉ የነበሩ ውስጠ - ሌላ ሰዎች መሆናቸው በተለያዩ ሚድያዎች በስፋት ተዘግቧል:: እየተዘገበም ነው::
በቅርቡ በኢቢኤስ በሚተላለፈው የቴሌቪዝን መርሓ ግብርም ላይ በግልጽ የቤተ ክርስትያኒቱን ዘመን - ጠገብ ዜማዎችና የተከበሩ ዘማርያንን "መንደርተኛ " እስከማለት ደርሰዋል :: ይህ በሃይማኖት ነጻነት ስም የሚጫር ጠብ አጫሪነት በጊዜ ካልተፈታ በኋላ ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሀገራዊ ችግር መፍጠሩ አይቀርም::
To EBS
ስለዚህ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ጥያቄዎቻችንን ከዚህ በታች አቅርበናል::
1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ራሱን የቻለ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ መዋቅር አላት:: ማንኛውም የቤተክርስትያኒቱን ስም ይዞ የሚወጣ የአየር ፕሮግራም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ ፈቃድ ወይም ይሁንታ ማግኘት አለበት:: ወይም የቤተክርስትያኒቱ ህጋዊ መዋቅር ውስጥ ያለ አካል መሆን ይኖርበታል:: ቤተ ክርስትያኒቱ ያላከችው ማንም አካል ግን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ስም ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም::
በዚህም መሰረት ታዖሎጊስና ቃለአዋዲ የተሰኙት መርሓ ግብሮች ከቤተ ክርስቲያኗ ህጋዊ ፈቃድ እስካልተሰጣቸው ድረስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ስም መጠቀም አይችሉም:: ስለዚህም ከቤተ ክርስትያኒቱ አስተዳደር ህጋዊ የሆነ ማስረጃ ካላመጡ በስተቀረ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም መጠቀም እንዲያቆሙ ቴሌቪዝን ጣብያው አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድልን እንጠይቃለን::
2. በነዚሁ የቴሌቪዝን መርሓ ግብሮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና በሚጥስ መልኩ የሚተላለፉ መልክቶችና ድርጊቶች እየተበራከቱ መጥተዋል:: ይህም የአንድን ሃይማኖት ክብርና ልዕልና የሚነካ ነው::ለምሳሌ ለመጥቀስ - በየትኛውም ኦርቶዶክሳዊ መስፈርት የእመቤታችን ስዕል ከአትራኖስ ስር አትቀመጥም:: እንዲህ አይነት በኦርቶዶክስ ስም የሚከናወኑ ኢ - ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ስብከቶችና ድርጊቶች የሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ የሞራልና የስነ ልቦና ጫና እያስከተለ ነው:: ሕዝቡ ወደ ሕጋዊ ጥያቄ ከመሄዱ በፊት የኢቢኤስ አስተዳደር አስፈላጊውን እርምት እንዲሰጥልን እንጠይቃለን::
3. በነዚሁ ሰባክያን በነዚሁ ቴሌቪዝን መርሃ ግብሮች ላይ ባደባባይ " መንደርተኛ " በሚል የተዘለፈው የቤተ ክርስትያኒቱ ዘማሪ ይልማ በይፋ ይቅርታ እንዲጠየቅና ድጋሚም በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮም ሆነ መምህራን ላይ ተመሳሳይ ዘለፋ እንዳይከናወን አስፈላጊውን መመርያ እንዲሰጥልን የኢቢኤስን አስተዳደር በኢትዮጵያዊና ክርስትያናዊ ትህትና እንጠይቃለን::
4. በመጨረሻም እነዚሁ ስብስቦች ለቲቪ ፕሮግራሞቻቸው ማስፈጸሚያ ይሆኑ ዘንድ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ስም የሚያደርጓቸው የስፓንሰር ጥያቄዎችና ልመናዎች በአስቸኳይ እንዲታገዱ እንጠይቃለን::
በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አስተዳደርም፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ስለሚተላለፉት መርሓ ግብሮች ግልጽ መግለጫ እንዲሰጥ እንጠይቃለን::ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ታሪክ : ዶግማና ቀኖና ከመጠበቅ እና ከማስጠበቅ አንጻር በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊው ምዕመን ዘርፈ -ሰፊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እንጠይቃለን.
You can further help this campaign by sponsoring it
The ታዖሎጎስና ቃለ አዋዲ የተባሉ የቲቪ ፕሮግራሞች በኦርቶዶክስ ስም እንዳይጠቀሙ ስለመጠየቅ petition to EBS (Ethiopian Broadcasting TV), Ethiopian orthodox church patriarch was written by Reda Wube and is in the category Religion at GoPetition.