#Sports
Target:
Ethiopian Football Federation
Region:
GLOBAL

የወልድያ እግር ኳስ ቡድን ሀገሪቱ ዉስጥ ከሚገኙ ክለቦች ሁሉ እጅግ ያማረ እና የፊፋን አለም አቀፍ መሥፈርት ያሟላ ስታድየም በመያዝ የሚወዳደረዉ ክለብ የለም!!....ክለቡም በጠንካራ የመከላከል አጨዋወት ዘይቤ የሚታወቅ መልካም የሚባል ጅማሮ በ2010 ዓ.ም በፕሪሚየር ሊጉ ላይ አሳይቶን ነበር!!...ሆኖም ግን ክለቡ የጨዋ ደጋፊ ባለቤት መሆኑ ፣ የአለምአቀፍ ደረጃን ያሟላ ስታዲየም ባለቤት መሆኑ እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ተሽሎ መገኘቱ ያላስደሠታቸዉ ግለሰቦች በክለቡ ላይ በሸረቡት ሴራና ያን ተከትሎ በወልድያና በአካባቢው በተፈጠረ የነፃነት ናፋቂ ህዝብ ና የጨቋኝ መንግስት አለመግባባት አንዲሁም ጅምላ ግድያ ምክንያት አብዛኛውን የአመቱን ክፍለ ጊዜ ተጫዋቾችና ክለቡ ያለዉድድር ማሳለፋቸዉ ይታወቃል!!...ይህም አልበቃ ያላቸዉ ሴረኞችና የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ጋጠወጥ ጥቅም ፈላጊ ካድሬዎች ከሰሞኑ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገዉ ፍፁም ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት የታየበትን ጨዋታ ሰበብ አድርገዉ በደጋፊዎቹ ባለቀ ደቂቃ በተከሰተ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት በክለቡ ላይ የተጣለበት የቅጣት ዉሳኔ አስቂኝ አሳዛኝና አሳፋሪ መሆኑን ሳልጠቅስ አላልፍም!....በሀገሪቱ የከፍተኛውም ሆነ የሌሎች እግር ኳስ ጨዋታዎች ታሪክ በተፈጠሩ የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደሎች ላይ ይህን ያክል ቅጣት የተጣለበት ክለብ አላየሁም አልሰማሁም!....ወልድያ ግን የሰሚዉን ጆሮ ጭዉ የሚያደርግ የክፍለዘመኑ ታላቅ ቅጣት ተጣለበት!....ወልድያ ላይ የተፈጠረዉ መለስተኛ መረባበሽ ከዚህ ቀደም ከተፈጠሩት ሁሉ እጅግ ትንሹ ሆኖ ሳለ የተጣለበት ቅጣት ግን ድሮም እፈልግሽ ነበር እንኳን ደህና መጣሽ የሚያስመስልበትን ፍርደ ገምድልነት ፌዴሬሽኑ ላይ ተመልክተናል!! ወልድያ በፕሪሚየር ሊጉ ተወዳድሮ አመቱን በመሪነት ቢያጠናቅቅ እንኳን የሚሸለመዉ ሽልማት 150,000 ብር ብቻ ነዉ!...ለትንሽ መረባበሽ ግን 250,000 ሺህ ብር ቅጣት ፣ ተጎዱ ለተባሉ አካላት ሙሉ የህክምና ወጪ እንዲሸፍን ፣ ታላቁ ስታዲየም እንዲዘጋ ፣ አሰልጣኙ ከስልጠና እንዲታገድ ፣ ተጫዋቾች እንዲታገዱ ፣ በአጠቃላይ የክለቡን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ አሳዛኝ ዉሳኔ እንደተወሰነበት ሰማን! ሰምተንም ተመለከትን!....ይህ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለዉ ዉሳኔ በተባበረው የህዝብ ሐይል እንቀለብሰዋለን ።

እኛ ይህንን ማመልከቻ የፈረምነው ፌደሬሽኑ የወሰደውን አላስፈላጊ ውሳኔ በአስቸኳይ ያነሳ ዘንድ ነው ።

GoPetition respects your privacy.

The ፍትህ ለ ወልዲያ እግርኳስ ቡድን petition to Ethiopian Football Federation was written by and is in the category Sports at GoPetition.